Back to blog

ከግብር ከፋዮች ለ2018 ዓ.ም ለሚቀርቡ የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች በኦንላይን ሲስተናገዱ በኢሜይል ሊላኩ የሚገባቸው ሰነዶች

ለ2018 ዓ.ም የታክስ ሂሳብ መግለጫ በኦንላይን ለሚስተናገዱ ግብር ከፋዮች በኢሜይል ሊላኩ የሚገባቸው ሰነዶች

ለ2018 ዓ.ም የታክስ ሂሳብ መግለጫ በኦንላይን ለሚስተናገዱ ግብር ከፋዮች በኢሜይል ሊላኩ የሚገባቸው ሰነዶች

ከግብር ከፋዮች ለ2018 ዓ.ም ለሚቀርቡ የታክስ ሂሳብ መግለጫዎች በኦንላይን ሲስተናገዱ በኢሜይል ሊላኩ የሚገባቸው ሰነዶች

የሚከተለው ዝርዝር ለ2018 በጀት ዓመት (ከሐምሌ 1/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም) የታክስ ሂሳብ መግለጫ በኦንላይን ለሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለሁሉም የንግድ ዘርፎች የሚጠበቁ ሰነዶችን እና በዘርፍ ባህሪ የሚቀርቡ ተጨማሪ ሰነዶችን ያካትታል።

1ኛ) ከሁሉም ዘርፎች የሚጠበቁ ሰነዶች

ሀ) የሂሳብ እና የውጭ ኦዲተሮችን በተመለከተ

የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ (ኢሜይል እና ስልክ ቁጥር)
የታደሰ የሙያ ፍቃድ
ተቀጣሪ ከሆነ ቢያንስ 3 ወር የከፈሉበት ፔይሮል እና የቅጥር ውል (ኢሜይል እና ስልክ ቁጥር ጨምሮ)

ለ) በሁሉም የንግድ ስራ ዘርፎች ከንግድ ስራ ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ሰነዶች

የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ሽት /Cash Count/
በእጅ ላይ ያሉ የንግድ እቃዎች ቆጠራ ሽት /Beginning and Ending Inventory Count Sheet/
ባንክ ሪኮንሲሌሽን /Bank Reconciliation/
ባንክ መግለጫዎች /Bank Statements/ በማህተም የተደገፈ።
Peachtree Backup
Peachtree ለማይጠቀሙ ከሌሎች ሶፍትዌር ወደ E-Xcell የተዛወረ ሌጀር።
ከሽ/መ/መሳሪያ የወጣ ጆርናል በሲዲ /CD-Copied Journal/
የሽ/መ/መሳሪያ የወጣ ዓመታዊ የሽያጭ ማጠቃለያ /Sales Summary By Each Cash Register Machine/ እንዲሁም የማንዋል ሽያጭ (የዱቤ እና እጅ በእጅ) በየደረሰኙ ቅድመ-ተከተል በመዘርዝር በሶፍት ኮፒ ይቅረብ።
እያንዳንዱን ግዥ እና ሽያጭ ከሐምሌ 1/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም በወራቶች ቅድመ-ተከተል ከነመለኪያ፣ የስሪት ሀገር፣ የእቃ ብዛት፣ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ የያዘ ዝርዝር በሶፍት ኮፒ መቅረብ አለበት።
የአገር ውስጥ ለተፈጸመ ግዥ ደረሰኞች ስካን ተደርጎ።
ከአገር ውስጥ ግዥ ሲፈጽሙ ዊዝሆልዲንግ ታክስ ደረሰኝ (ከአቅራቢው የተሰጠ) ከሂሳብ መግለጫ ተሰብሳቢ ጋር የተመሳከረ የደረሰኞችን ዝርዝር — አቅራቢው ስም እና ቲን የያዘ፣ ከነገንዘብ መጠኑ እና ደረሰኝ ቀናትን ያካተተ ሰንጠረዥ።
ከውጭ ሀገር ግዥ ወቅት ለጉምሩክ የተከፈለ ዊዝሆልዲንግ ከላይ ከተጠቀሰው ከአገር ውስጥ ግዥ ዊዝሆልዲንግ ዝርዝር ጋር ተካትቶ መቅረብ ይችላል።
ለ2018 ግብር ቅድመ-ታክስ ለገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት የተከፈለበት ደረሰኞች።
ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና ለዓመታዊ (የንግድ ትርፍ ግብር እና ኪራይ ገቢ) ሽያጭ የታረቀበት/የተመሳከረበት/ መሳያ ሰነድ።
ወደ ባንክ ገቢ የተደረጉ ነገር ግን የዓመቱ ሽያጭ አካል ያልሆነ (RTGS, Loan & ETC…) በዝርዝር በመለየት በቅጽ ማሳወቅ።
ባንክ ገቢ የተደረገ ገንዘብ ከዓመታዊ ሽያጭ እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ሽያጭ ጋር የታረቀበት /Bank Credit Vs with sales/ ማሳያ።
የመጋዘን ኪራይ ውል ወይም ደረሰኝ መቅረብ አለበት።
ከአንድ ዘርፍ በላይ ላላቸው ግብር ከፋዮች በተናጠል የተዘጋጀ ትርፍ እና ኪሳራ መግለጫ በማህተም የተደገፈ፣ ከማሳወቂያ ቅጹ ጋር ተመሳሳይ ስለመሆኑ የተመሳከረ ስካን ተደርጎ።
የታክስ ሂሳብ መግለጫ ሲቀርብ Balance Sheet, Statement of Profit or Loss, Cash Flow Statement እና Statement of Equity መካተት አለባቸው።
የብድር ውሎች፣ የባንክ ብድር እና ከባንክ ብድር ውጭ ላሉ ብድሮች ቴምብር ቀረጥ የተከፈለባቸው ውሎች መሆን ይገባቸዋል።
የቤት ኪራይ ወጪ በሰነዶች ማረጋገጫ የጸደቀ ወይም በደረሰኝ የተገለጸ።
የወለድ ወጪ ማሳያ /Bank Loan Statement/።
የግብር እፎይታ /Tax Holiday/ የተፈቀደለት ከሆነ ለዚሁ የተሰጠ ደብዳቤ።
ኪራይ ገቢ እና ሌላ ተጨማሪ ዘርፍ ያላቸው ግለሰብ ግብር ከፋዮች የትርፍ እና ኪሳራ መግለጫ (በሰንጠረዥ "ለ" እና "ሐ") በተናጠል ሊያቀርቡ ይገባል።
የሚሸጡ እቃዎች /Trading Stocks/ የስቶክ እንቅስቃሴ /Stock Status Report/ — ገቢ፣ ወጪ እና ቀሪ ባላንስ የሚያሳይ ሪፖርት በሶፍት ኮፒ መቅረብ አለበት። ሃርድ ኮፒ ከሆነ ስካን ማድረግ ይቻላል።
የተበላሹ እቃዎች በወጪነት ተመዝግበው ከሆነ ከተቆጣጣሪ አካላት ወይም ከገቢ ሰብሳቢው መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ።
በታክስ ሂሳብ መግለጫ ላይ Owners Account, Account Receivables, Trade Receivables, Sundry Receivables እና Other Receivables እና መሰል ያሉ የተመዘገቡ ተሰብሳቢ ሂሳቦች የታክስ ሂሳብ መዝገብ /Ledger/ ላይ የሚሰበሰበው ከነማን እንደሆነ በስም ተዘርዝሮ መታየት ያለበት ነው። ሆኖም ሌጀር ይህን በግልጽ የማያሳይ ከሆነ ከባለፈው ዓመት የዞረውን/የተሻገረውን ጨምሮ የበጀት ዓመቱ በዝርዝር መቅረብ አለበት።
በታክስ ሂሳብ መግለጫ ላይ Account Payables, Loan Payables, Trade Payables, Sundry Payables, Other Payables, Owners Account እና መሰል ያሉ የተመዘገቡ ተከፋይ ሂሳቦች የታክስ ሂሳብ መዝገብ /Ledger/ ለማን እንደሚከፈል በስም ተዘርዝሮ መታየት ያለበት ነው። ሆኖም ሌጀር ይህን በግልጽ የማያሳይ ከሆነ ከባለፈው ዓመት የዞረውን/የተሻገረውን ጨምሮ የበጀት ዓመቱ በዝርዝር መቅረብ አለበት።

2ኛ) በዘርፍ ባህሪ አንጻር የሚቀርቡ ተጨማሪ ሰነዶች

ከላይ የተዘረዘረው ለሁሉም የንግድ ዘርፎች መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከሚከተሉት የንግድ ዘርፎች ባህሪ አንጻር የሚቀርቡ ተጨማሪ ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው።

ሀ) አስመጪዎችን በተመለከተ

የእቃ ዋጋ ግንባታ ማሳያ /Cost Sheet by each Declaration & item/
የጉምሩክ ዴክለራሲዮኖች ኮፒ — ስካን ተደርጎ።
አስመጪዎች እቃዎች ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ የታየ የውጭ ምንዛሬ /Import Foreign Currency/ ልዩነት በምዝገባ ለይቶ ማሳየት።

ለ) ላኪዎች

ዕቃው ወደ ውጭ ስለመላኩ የጉምሩክ ዴክለራሲዮኖች።
የኤክስፖርት እቃ ተሽጦ ገንዘቡ ወደ ብሔራዊ ባንክ ስለመግባቱ ማሳያ።
የውጭ ሀገር ዴክለራሲዮን ላይ የተመላከተ እና ብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደረገ ወደ ውጭ የተላከ የእቃ ሽያጭን የተመሳከረበት /Sales Reconciliation/።
ወደ ውጭ የሚላኩ እቃዎች የተገዙበት ሁኔታ — በትስስር፣ በኮንትራክት ፋርሚንግ እና ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሊሆን ይችላል።
በኮንትራክት ፋርሚንግ ከሆነ የምርት ኪራይ ውል ሰነድ፤ በትስስር /Vertical Integration/ ከሆነ እና በግዥ ማረጋገጫ /Purchase Voucher/ የተገዛ ከሆነ የግዥ ክፍያው ወደ ባንክ ስለመተላለፉ እና በግዥ ማረጋገጫ የተገዙበትን ደረሰኞች ሊቀርቡ ይገባል።

ሐ) ህንጻ ኪራይ እና መጋዘን ኪራይን ጨምሮ

በግዥ የተገኘ ህንጻ/ቤት ከሆነ የግዥ ደረሰኝ ወይም በህግ ፊት የጸደቀ ውል።
ህንጻው ዋጋ በባለሞያ /ህንጻ ገማች/ የተገመተ ከሆነ የግምት ሰነድ።
የህንጻ ገማቹ የወቅቱ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የታደሰ የሙያ ፍቃድ።
በራስ የተገነባ ህንጻ እና በገማች ባለሞያ ዋጋው ያልተገመተ ከሆነ የግንባታ ዋጋው በግልጽ በታክስ ሂሳብ መዝገብ የሚታይ መሆን አለበት።
የእርጅና ቅናሽ ስሌት ማሳያ።
በራስ የተገነባ ህንጻ ከሆነ የመጠቀሚያ ፍቃድ እና የግንባታ ፍቃድ ያስፈልጋል።
በኪራይ ወቅት ያልተከራዩ ክፍሎች ካሉ ማሳያ ሰነድ።
ህንጻው ለንግድ፣ ለኪራይ እና ከንግድ ዓላማ ውጭ የሚውል ካለ ተለይቶ በካሬ ሜትር መቅረብ አለበት።
የተከራዮች የኪራይ ውል፤ በየጊዜው የውል እድሳት ካለ ይቀርባል። ውል የተቋረጠ ከሆነ ማስረጃ ያስፈልጋል።
ቤት ተከራይቶ የሚያከራይ ከሆነ የተከራየበትን እና ተከራይቶ ያከራየበትን የቤት ኪራይ ውል /ወይም ደረሰኞች/።
ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አክስዮን ማህበር የቤት ኪራይ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች የደመወዝ ወጪ ፔይሮል /Payroll/ ለኪራይ ገቢው የዋለው ብቻ ተለይቶ መቅረብ አለበት።

መ) ኮንስትራክሽን

ከአንድ ፕሮጀክት በላይ ከሆነ ለየፕሮጀክቶቹ የታክስ ሂሳብ መዝገብ መቅረብ አለበት።
የኮንትራክት ውሎች፣ የሰብ ኮንትራክት ውሎች፣ የኮንስትራክሽን ግንባታ ውል ማሻሻያዎች።
በየፕሮጀክቶቹ የተዘጋጀ የክፍያ ምስክር ወረቀቶች /Interim Payment Certificate/።
የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ካሉ /Final Payment Certificate/።
የዓመታዊ ገቢ ለማሳወቅ /Percentage of Completion of Revenue Recognition/ ስሌት ማሳያ።
የ2017 በጀት ዓመት እና ከዚያ በፊት የነበሩ እና በ2018 በጀት ዓመት የተላለፉ ፕሮጀክቶች ከሆኑ በ2017 በጀት ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ የተሰጡ/የጸደቁ የክፍያ የምስክር ወረቀቶች /Interim Payment Certificates/።
የግንባታ የውል ሰነድ ከነማሻሻያ /Contract Document with amendment if any/።
ከመንግስት ፕሮጀክቶች ጋር በተገባ የግንባታ ውል ላይ ከሆነ እና የታወቀ/የተተመነ የትርፍ ህዳግ ካለው ይህንን ሊገልጽ የሚችል ሰነድ መቅረብ አለበት።

ሠ) ማሽነሪ ወይም መኪና ኪራይ

ኪራይ ላይ የተሰማሩ ማሽነሪዎች ስራ ላይ ስለመሆናቸው የሰዓት መቆጣጠሪያ ሽት /Equipment Utilization Hour Sheet/።
የተከራይ እና አከራይ የማሽነሪ ኪራይ ውል።
የኪራይ ማሽነሪ ጥገና ላይ ወይም በሌላ ምክንያት ስራ ያልሰራበት ቀናቶች ካሉ ይህንን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
ተከራይቶ ማከራየት ከሆነ የኪራይ ውል።
የራስን ማሽነሪ/መኪና ማከራየት ከሆነ የኪራይ ውል።

ረ) በኮሚሽን ስራ ላይ ለተሰማሩ ግብር ከፋዮች

ከመንግስት ወይም ከግል ተቋማት የመሸጫ እና የመግዣ ዋጋ የተተመነላቸው/የተወሰነላቸው የንግድ እቃዎች ከሆኑ ይህንን የሚገልጽ ማሳያ የውል ሰነድ።

ሰ) አምራች

የስታንዳርድ ኮስት /Standard Cost Per Unit of Item/ ማሳያ።
የማምረቻ ወጪ ማሳያ /Cost of Goods Manufactured/።
በዓመቱ መጨረሻና መጀመሪያ የተመረቱ/በሂደት ላይ ያሉ እና ጥሬ ዕቃዎች ቆጠራ ዝርዝር።
የጥሬ ዕቃዎች ቫሉዌሽን ሽት እና የተመረቱ ዕቃዎች መግለጫ።
የኤክሳይዝ ታክስ ማሳወቂያ።

ሸ) ሪል እስቴት

የገቢ /Revenue Recognition/ — Percentage of Completion ወይም Completed Contract Method መሰረት እንደየ ሪል እስቴቱ የአገነባብ ሁኔታ (በራስ ወጪ የተገነባ ወይም ቅድመ-ክፍያ ከደንበኞች የተሰበሰበ እና ከደንበኞች ጋር የተገባ ውል ስምምነት ስለመኖሩ) ስሌቱን የሚያሳይ።
የዓመታዊ ገቢ ለማሳወቅ Percentage of Completion of Revenue Recognition የሚጠቀሙ ከሆነ የዚህን ስሌት ማሳያ።
የዓመታዊ ገቢ ለማሳወቅ Completed Contract Method of Revenue Recognition የሚጠቀሙ ከሆነ የዚህን ስሌት ማሳያ።
ሪል እስቴቱ የሚገነባው በሌላ ኮንትራክተር ከሆነ የግንባታ ውል።
ከቤት የሚገዙ ደንበኞች ጋር የተፈራረሙት የቤት ሽያጭ ውል (በድጋሜ የተሻሻለ ከሆነ የተሻሻለውን ውል ጨምሮ)።
ሪል እስቴት አጠናቆ የሚያከራይ ከሆነ የተከራዩትን ቤቶች ዝርዝር እና የኪራይ ውል መቅረብ ይኖርበታል።

ቀ) የትራንስፖርት ዘርፍ

የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ለመስጠት የአገልግሎት ውል ካለ የውል ሰነድ።
የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ /Libre/።
የእርጅና ቅናሽ ስሌት ማሳያ።
ከዚህ ቀደም የትራንስፖርት ግብር በቁርጥ ወይም በሂሳብ መዝገብ ይከፍሉ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማብራሪያ።

በ) ጅምላ እና አከፋፋይ ንግድ

እያንዳንዱን ግዥ እና ሽያጭ ከሐምሌ 1/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም በወራቶች ቅድመ-ተከተል ከነመለኪያ፣ የስሪት ሀገር፣ የእቃ ብዛት፣ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ የያዘ ዝርዝር በሶፍት ኮፒ መቅረብ አለበት።
ከዚህ ቀደም አድቫንስ ክፍያ ፈጽመው እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ የተገዙ እቃዎቹ ያልደረሳቸው ከሆነ ቅድመ-ክፍያ የተፈጸመበት ደረሰኝ ኮፒ።

ቨ) ችርቻሮ ንግድ

እያንዳንዱን ግዥ እና ሽያጭ ከሐምሌ 1/2017 እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም በወራቶች ቅድመ-ተከተል ከነመለኪያ፣ የስሪት ሀገር፣ የእቃ ብዛት፣ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ የያዘ ዝርዝር በሶፍት ኮፒ መቅረብ አለበት።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ዝርዝር ለአጠቃላይ መረጃነት የቀረበ ሲሆን ግብር ከፋዮች የመጨረሻ እና ወቅታዊ መመሪያ ከሚመለከተው የገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።